ስጋህን ስንቴ አሽንፎህ ያውቃል?
ለልዑልሰገድ
ስሙኝማ
ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ
እንዲህ የሚል ነገርን አየሁ። ሮሜ 7:
14-20 "እኔ
ግን ከሀጢያት በታች ልሆን የተሽጥኩ የስጋ
ነኝ። የማደርገውን አላውቅምና የምጠላውን
ያን አደርጋለሁ። ዳሩ ግን የምወደውን የምወደውን
እርሱን አላደርግም። የማልወደውን የማደርግ
ከሆነ ህግ መልካም እንደሆነ እመሰክራለሁ።
እንደዚህ ከሆነ ያን የማደርገው አሁን እኔ
አይደለሁም፣ በኔ የሚያድር ህግ እንጂ። ብስጋዬ
በጎ ነገር እንደማይኖር አውቃለሁ። የስጋ
ፈቃድ አለኝ። መልካሙን ማድረግ የለኝም።
የማልወደውን ክፉውን ነገር አደርጋለሁ። "
እያለ
የመልክቱ ጸሃፊ ይቀጥላል። "
እናስ?”
አትሉኝም።
ይህ ሰው እኔን የሚያውቀኝ ውይም እኔ ማለት
የፈለኩትን ነገር ያለ ይመሰለኝና ድንገጥ
እላለሁ። ብዙ ጊዜ አስተውላችሁ ከሆነ የምንገኘው
በጣም በምንጸየፈው "ሲስተም"
ውስጥ
ነው። ለምሳሌ አታመንዝር የሚለውን ጽሁፍ
ማታ አንብበነው ጠዋት አይናችን ሲቀላውጥ
የምራቅ እጢያችን ከቀድሞው በበለጠ ስራውን
ሲያፋጥን እናየዋለን።
መዳራት
ሀጢያት መሆኑን ተነግሮን ካፌ ውስጥ ተቀምጠን
በአይናችን አጭር ቀሚስ ያደረገችን ሴት
እናሽኮረምማለን። ጉንጭ የምንስም መስለን
ከንፈር ጨረፍ አድርገን እናልፋለን። የሃጢያት
በር መሆኑን ልባችን እየነገረን በፌስቡክ
ስለ እምነት እያወራን በ "ዩ
ቲዩብ" ደግሞ
'ፖርኖግራፊ"
ለማየት
አይናችንን እናፈጣለን። በዝምታ ውስጥ ሰላም
እንዳለ እያወቅን ወደ ናይት ክለብ ጎራ ብለን
ጆሯችንን እንበጠብጠዋለን። በጎናችን የራሳችንን
አቅፈን የሌላ ሴት እናሽኮረምማለን። በስርአት
ነግደን ማትረፍ ስንችል አጭበርብረን መክበር
እንሻለን። አረ ስንቱ....!!
በነገራችን
ላይ ሴቶችም ከዚህ ነጻ አይደላች ሁም።
በእርግጠኝነት እደግመዋለሁ እናንተም ከነዚህ
ነገሮች የብዙው ባሪያዎች ናችሁ። ማንም ሰው
እራሱን ከስጋ ፍላጎት ነጻ መውጣት አይችልም።
ስጋ ሁሌም ስጋ ነው። ምኞቱ ሁሌም አያልቅም።
ምኞቱም ምክንያታዊ ነው። ለምሳሌ በስርአት
ተቀምጠህ የነበርከው ሰውዬ እርዝመቱ ከዳሌዋ
በላይ የሆነ ቀሚስ ያደረገች ውብ ሴት በአጠገብህ
ስታልፍ ስጋህ ባላሰብከው መንገድ ይተናኮልሃል።
"እያት
አታምርም ባትዋን ጭንዋን እየው አቤት የአንተ
ብትሆን!!" ይልሃል።
የልጅ
አባት ልትሆን ትችላለህ። ሚስትህን ትዳርህን
አክባሪም ልት ሆን ትችላለህ ግን እመነኝ ስጋህ
የምኞት ባሪያ ስለሆነ ለስከንዶችም ቢሆን
ሚስትህንና ልጅህን ያስዘነጋ ሃል። የምትነቃው
ከሰከንዶች በህዋላ ስለሚሆን መወስለትህን
አታውቀውም።
ወደድክም
ጠላህም ፓውሎስ እንዳለው ሁለት አንተነቶች
በውስጥህ አሉ። አንደኛው ስለፍቅር ሲሰብክህ
ሌላው በወሲብ ስለሚገኘው ደስታ ያወራልሃል።
አንደኛው ማንነትህ ስለቅድስና ሲያወራህ
ሌላኛው ማንነትህ ደግሞ "ዝም
በለው ይሄ ወሬኛ"
ይልሃል።
በነገራችን
ላይ በአንተ አይፈረድም ስጋህ ተቆጣጥሮሃል።
የምኞት ተገዢ አድርጎሃል ምን ሃይማኖተኛ
ብትሆን የስጋ ነገር አይለቅህም።
በሚያስደስት
የወንጌል ስብከት ላይ ተገኝተህ ነፍስህ
ስትፈነጥዝ በአጋጣሚ የምትወደው "ስፕሬይ"
ከየት
እንደመጣ ሳይነግርህ ወደ አፍንጫህ ይገባል።
"የማን
ይሆን?” ብለህ
ጥሩ ልብስ የለበሰች እንስት ስትፈልግ ከፊት
ባለው ወንበር ላይ ጸጉርዋ ትከሻዋን የሸፈናት
ሴት ላይ አይንህ ያርፋል። ከዛም የቀድሞውን
የስፕሬይ ታሪክ ትረሳና "ጸጉርዋ
ነው ወይስ አርቴፊሻል?”
ብለህ
መፈላሰፍ ትጀምራለህ። ምክንያቱም ስጋ መፈላሰፍ
ይወዳላ!! አንተ
ግን እኮ ለራስህ የማሃላ መአት ደርድረህ
አይንህ እንደማያመነዝር ቃል ገብተህ ነበር።
ያኛው አንተነትህ ግን ተፈጥሮን ውበትን ማድነቅ
በሚል ብሂል ያስመነዝር ሃል።
እና
መፍት ሄው ምን ይመስልሃል?
እኔ
መልሱን አግኝቼዋለሁ እስቲ አንተ ሞክረው
አንቺ ሞክሪው!!!
በነገራችን
ላይ ይህንን ጽሁፍ የምታነብ/ቢ
ሁላ በተአምር እራስህን/እራስሽን
ነጻ አድርገሽ/ አድርገህ
አንዳታይ ይህ እራሱ የስጋ ጉራ ነው !!!
በመጫረሻም
ጳውሎስን አመስግኑልኝ እሱ ይህንን ጥያቄ
ባይጠይቅልኝ ኖሮ ማን ይጠይቅልኝ ነበር?
እሱ
ግልጽ ባይሆን ኖሮ ማን ግልጽ ሆኖ ይነግረኝ
ነበር?
Comments
Post a Comment