"በሽታ የሌለበት ቅጥነትና እዳ የሌለበት ድህነት ሀብት ናቸው”


"በሽታ የሌለበት ቅጥነትና እዳ የሌለበት ድህነት ሀብት ናቸው” ከብሩክ የታክሲ ባለቅኔው የተዋስኳት ምርጥ አባባል። እውነት አይደል ግን? እንደ ዳርት ተወርዋሪ ቅጥነት፣ እንደ እንዝርት ተሽከርካሪ ማን ነት ይዞ በጤና መኖር ከተቻለ ስጋን መሽከም ምን አመጣው።
እኔ ከምነግራችሁ በላይ በጣም ቀጫጫ ነኝ። የሃገሬ ኢኮኖሚ በደብል ዲጂት ወደላይ ተሽቀንጥሮ ሲያድግ የኔ ኪሎና የኔ ውፍረት ግን ላለፉት አስር አመታት ባለበት ነው። ግን አምላክ ይመስገን ባለፉት አመታት በሽታ በመንገድ ላይ ሲያልፍ ቅጥነቴ አልታይ ብሎት ነው መሰለኝ አንድም ቀን ሰላም ብሎኝ አያውቅም።
የድህነትዋ ጉዳይ ግን እራስን መሸወጃ ትመስለኛለች። ምክንያቱም እዳ የሌላት ድህነት ልመና ብቻ ናት። ስትለምን አትበደርም፤በቃ አንተ ለማኝ ነህ። ማንም ካንተ ምንም አይጠብቅም።
ይቺ እዳ የሚልዋት ነገር የኔም የሃገሬም ባህሪ ሰሆነች አይደንቀኝም። ሀገሬ ለብዙ ጉዳዮቿ ትበደር የለ? ያለ እዳ አስፋልት ይሰራል? ያለ እዳስ ኮዶሚኒየም ይገኛል? እዳ የእድገት መሰላል ናት። እዳህን ለማወራረድ ትፍጨረጨራለህ። ትወጣለህ ትወርዳለህ፣ ለአለቃህ ታሸረጉዳለህ፣ ላላመንክበት ነገር ምስክር ት ሆናለህ። እንደ ሃገሬ አይነት ባለሃብት ከሆንክ ደሞ በእዳ ማርቼዲስ ትገዛና ደሃው ወዳጅህ ላይ ታነጅ ብበታለህ፣ እስቲ እዳ የሌለበት ኢትዮጵያዊ የቱ ነው? ግማሹ የገንዘብ ባለ እዳ ሲሆን ሌላው ደግሞ የእንባ ባለ እዳ ነው:: ሌላው ደግሞ የእውቀት ባለ እዳ ነው። ሌላ ሌላውን የእዳ አይነት ለናንተ ትቼዋለሁ።

Comments

  1. ከመበደር አትቦዝን ለመክፈል አትችኩል ቢቻልህ ለመካድ ሞክር

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular Posts