ቪዛ የተከለከልኩ ቀን
በነገራችን ላይ ቪዛ መከልከል ለጊዜው ቅስም ቢሰብርም ፍጹም ሀገር ወዳድ እንደሚያደርግ የደረሰበት ያውቀዋል.....😂😂😂😂.....
የአሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ከልክሎህ ስትወጣ መጀመሪያ አይንህን ፈጣሪህ ላይ ታጉረጠርጣለህ....ከዛ እድልህን መራገም ትጀምርና ለኮቴ የከፈልከው ዶላር ትዝ ሲልህ ከሽሮሜዳ አራት ኪሎ ለብቻህ መንገድ ላይ እየለፈለፍክ ትጓዛለህ.....ከዛ ዶክመንትህን የሆነ ስርቻ ውስጥ ወርውረህ አሁንም የአርባ ቀን እድልህንና ሀገርህን መራገም ትጀምራለህ......"ለማኝ፣ የለማኝ ሀገር..." እያልክ ምንም ያልበደሉህን ህዝቦችና ደረቅ ጡቷን ግታ ያሳደገችህን ሀገር መስደብ ትጀምራለህ....😂😂😂
በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራቶች ውስጥ ጆሮህ የሚሰማው Sorry sir, we did not found your documents sufficent enugh to aquire the visa please try some other time የሚለውን ድምጽ ብቻ ስለሚሆን ጆሮህ ውስጥ ኢርፎን ሰክተህ ነው የምትውለው....😂😂😂😂በሚቀጥሉት ወራት በመጠኑ መረጋጋት ትጀምራለህ.....ከዛ ሀገርህ የ13 ወራት ባለጸጋ፣የወንዞችና የተራራዎች መገኛ፣ "የመቻቻል ምድር" ፣ የብሄር ብሄረሰቦችና የጄሶ እንጀራ መገኛ ምድር መሆኗ ትዝ ሲልህ በቃ ትጽናናለህ......ሀገርህን ማፍቀር ትጀምራለህ......ህዝብህን መውደድ ትጀምራለህ....."ኢትዮጵያ ሀገሬ ልምላሜሽ ማማሩ...." እያልክ ታንጎራጉራለህ.....አሜሪካንን መናቅ ትጀምራለህ.....🙈🙈🙈🙈.....ሁሌ ግን "ለኮቴ" የከፈልካት ዶላርና የቪዛ ኦፊሰሩ አጭር መልስ ከአይምሮህ አይጠፉም.....😂😂😂😂.....
Comments
Post a Comment