ጥበብ አድርባይ


ጥበብ አድርባይ

እንደ ጥበብ ማን አለ አድርባይ?ለመጣው ለሄደው እዩኝ ባይ
ከመጣው ጋር ደንሶ
ክብርን ጥሎ ጭራን ነስንሶ
ያኛውን አኮስ
ይሄኛውን ከሰማይ አድርሶ
ጥበብም አስመሳይ
ተጠባቢው ውሸት አማሳይ
ዛሬ ለዚህ ተቀኝቶ
ያንን በነገር ወግቶ
ለሆዱ አድር ባይ
ለከርሱ ነገር አቀባይ
በቡሩሽ በብእር ውሸት እየቀባ
በወጠረው ሽራ እንደ አዞ እያነባ
አስመሳይ ባለራእይ
ያላየውን ሚያሳይ
Artilo Gelgelo
Dec 19 2014

Comments

Popular Posts